ከተባባሪ አካላት ና ድርጅቶች ገንዘብን ለመሰብሰብ የሚያስችል ድህረ ገጽ በኢትዩጵያ ስራ እንደጀመረ ያውቃሉ?

agarfund logo

ይህ ድህረ ገጽ አጋርፈንድ ይባላል፡፡ በሀገር ቤት በሀገር ልጆች ሰላምቴክ ቢዝነስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ባለቤትነት የተሰራ ነው፡፡ይህ ድህረ ገጽ በልዩ ልዩ የታመነባቸው የግልም ሆነ የማህበረሰብ ችግሮች ገንዘብን በዲጂታል መንገድ ለማሰባሰብ የሚያስችል የቴክኖሎጂ ውጤት ሲሆን የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ፣የሙያማህበራት፣የስፖርት ክለቦች፣ለህክምና እና ለትምሀርት ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ግለሰቦች ፣የፈጠራ ስራ ይዘው መነሻ ካፒታልን ለማሰባሰብ የሚያስቡ የማህበረሰባችን ክፍሎች እና ሌሎችም በቀላሉ ከደጋፊ አካላትና ተባባሪ ግለሰቦች የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ የሚያሰባስቡበት በኢትዩጵያ በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነ ድህረ ገጽ ነው፡፡

ይህንን ስራም ወደ ስራ ለማስገባት ሰላምቴክ ቢዝነስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከ ኢፌድሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች   ኤጀንሲ እና ከሌሎችም ተባባሪ የፋይናነስ ተቋማት ጋር የመግባበቢያ ሰንድን በመፈራረምና እና የስራ ግንኙነትን በመፍጠር በቅርበት እየሰራ ይገኛል፡፡

በመሆኑም በኢትዩጵያ መቀመጫቸውን ያደረጉ ልዩ ልዩ ተቋማትና ግለሰቦች በታመነለት ምክንያት ድጋፍን ለማሰባሰብ በቀላሉ ወደ አጋርፈንድ ድህረ ገጽ በመግባት በነጻ መመዝገብና ዘመቻ መፍጠር ይችላሉ፡፡

በተለይም አሁን በኮሮና ስጋትን ለመመከት ለሚደረገው ጥረት የገንዘብ ድጋፍን በዲጂታል መልኩ ባሉበት ሆነው የሚያሰባስቡበት ና እያንዳንዱንም ድጋፍ የሚከታተሉበት ዘመናዊ ድህረገጽ  በመሆኑ በጎ አደራጎት ድርጅቶች ያለምንም ክፍያ በነጻ ለመጠቀም ይችላሉ፡፡

ለማንናውም ጥያቄና አስተያየት ድህረ ገጹ ላይ ባሉት አራማጮች በሙሉ ይጠቀሙ፡፡

www.agarfund.com

#አጋር እንሁን

#የአንዱ ትርፍ የሌላው ምኞት ነው!

#በጋራ እናልፈዋለን